Jeremiah 46

ስለ ግብፅ የተነገረ መልእክት

1ስለ ሕዝቦች ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

2ስለ ግብፅ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በአራተኛው ዓመት በኤፍራጥስ ወንዝ በከርከሚሽ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ባሸነፈው በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ኒካዑ ሰራዊት ላይ የተነገረ መልእክት ይህ ነው፤

3“ትልቁንና ትንሹን ጋሻ አዘጋጁ፤
ለውጊያም ውጡ!
4ፈረሶችን ጫኑ፤
በላያቸውም ተቀመጡ!
የራስ ቍር ደፍታችሁ፣
በየቦታችሁ ቁሙ፤
ጦራችሁን ወልውሉ፤
ጥሩራችሁን ልበሱ!
5ነገር ግን ይህ የማየው ምንድን ነው?
እጅግ ፈርተዋል፤
ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ነው፤
ብርቱ ጦረኞቻቸው ተሸንፈዋል፤
ዘወር ብለውም ሳያዩ፣
በፍጥነት እየሸሹ ነው፤
በየቦታውም ሽብር አለ፣”
ይላል እግዚአብሔር
6“ፈጣኑ መሸሽ አይችልም፤
ብርቱውም አያመልጥም፤
በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣
ተሰናክለው ወደቁ።

7“ይህ እንደ አባይ ወንዝ ሙላት የሚዘልለው፣
እንደ ደራሽ ወንዝ የሚፈስሰው ማነው?
8ግብፅ እንደ አባይ ወንዝ ሙላት ይዘልላል፤
እንደ ደራሽ ወንዝ ይወረወራል፤
‘እወጣለሁ፤ ምድርንም እሸፍናለሁ፤
ከተሞችንና ነዋሪዎቻቸውን አጠፋለሁ’ ይላል።
9ፈረሶች ሆይ ዘልላችሁ ውጡ፤ ሠረገሎችም ሸምጥጡ፤
ጋሻ ያነገባችሁ የኢትዮጵያና
የላይኛው አባይ አካባቢ ነው
የፉጥ ሰዎች፣
ቀስት የገተራችሁ የሉድ ጀግኖች፣
እናንተ ብርቱ ጦረኞች ተነሥታችሁ ዝመቱ።
10ያ ቀን ግን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤
ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን።
ሰይፍ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤
ጥማቱም እስኪረካ ድረስ ደም ይጠጣል።
በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷልና።

11“ድንግሊቱ የግብፅ ሴት ልጅ ሆይ፤
ወደ ገለዓድ ውጪ፤ የሚቀባ መድኀኒትም አምጪ፤
ነገር ግን መድኀኒት የምታበዢው በከንቱ ነው፤
ፈውስ አታገኚም።
12ሕዝቦች ኀፍረትሽን ይሰማሉ፤
ልቅሶሽም ምድርን ይሞላል።
ጦረኛ በጦረኛው ይደናቀፋል፤
ሁለቱም ተያይዘው ይወድቃሉ።”
13የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጥቶ ግብፅን እንደሚወጋ፣ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረው መልእክት ይህ ነው፤

14“ይህን በግብፅ ተናገር፤ በሚግዶልም አሰማ፤
በሜምፎስና
ዕብራይስጡ ኖፍ ይላል፤ 19 ይመ።
በጣፍናስም እንዲህ ብለህ ዐውጅ፤
‘በቦታችሁ ቁሙ፤ ተዘጋጁም፤
በዙሪያችሁ ያሉትን ሰይፍ ይበላቸዋልና።’
15ጦረኞችህ ለምን ተዘረሩ?
እግዚአብሔር ገፍትሮ ስለሚጥላቸው መቆም አይችሉም።
16ደጋግመው ይሰናከላሉ፣
አንዱም በሌላው ላይ ይወድቃል፤
‘ተነሡ እንሂድ፤
ወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ፤
ከጠላትም ሰይፍ እናምልጥ’ ይላሉ።
17በዚያም የግብፅን ንጉሥ ፈርዖንን፣
‘በተሰጠው ዕድል ያልተጠቀመ፣
አለሁ አለሁ ባይ ደንፊ!’ ብለው ይጠሩታል።”

18ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሡ እንዲህ ይላል፤
“በሕያውነቴ እምላለሁ”።
በተራሮች መካከል ያለውን የታቦር ተራራ የሚመስል፣
ባሕርም አጠገብ ያለውን የቀርሜሎስ ተራራ የሚመስል አንድ የሚመጣ አለ።
19እናንተ በግብፅ የምትኖሩ ሆይ፤
በምርኮ ለመወሰድ ጓዛችሁን አሰናዱ፤
ሜምፎስ ፈራርሳ፣
ሰው የማይኖርባት ባድማ ትሆናለችና።

20“ግብፅ ያማረች ጊደር ናት፤
ነገር ግን ተናዳፊ ዝንብ
ከሰሜን ይመጣባታል።
21ቅጥረኞች ወታደሮቿም
እንደ ሠቡ ወይፈኖች ናቸው፤
የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ፣
ጥፋታቸው ስለ ተቃረበ፣
እነርሱም ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ይሸሻሉ፤
በቦታቸውም ጸንተው ሊቋቋሙ አይችሉም።
22ጠላት ገፍቶ ሲመጣባት፣
ግብፅ እንደሚሸሽ እባብ ታፏጫለች፤
ዛፍ እንደሚቈርጡ ሰዎች፣
መጥረቢያ ይዘው ይመጡባታል።
23ጥቅጥቅ ጫካ ቢሆንም፣ ደኗን ይመነጥራሉ፤”
ይላል እግዚአብሔር
“ብዛታቸው እንደ አንበጣ ነው፤
ሊቈጠሩም አይችሉም።
24የግብፅ ሴት ልጅ ለኀፍረት ትጋለጣለች፤
ለሰሜን ሕዝብም ዐልፋ ትሰጣለች።”
25የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በቴብስ
ወይም ኖእ
አምላክ በአሞን ላይ፣ በፈርዖን ላይ፣ በግብፅና በአማልክቷ ላይ፣ በነገሥታቷም ላይ፣ እንዲሁም በፈርዖን በሚታመኑት ላይ ቅጣት አመጣለሁ፤
26ነፍሳቸውን ለሚሹት ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆርና ለጦር መኰንኖቹ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ግብፅ እንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር

27“አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤
እስራኤል ሆይ፤ አትሸበር፤
አንተን ከሩቅ ስፍራ፣
ዘርህንም ተማርኮ ከሄደበት ምድር አድናለሁ።
ያዕቆብም ተመልሶ በሰላምና በርጋታ ይቀመጣል፤
የሚያስፈራውም አይኖርም።
28አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል እግዚአብሔር
“አንተን የበተንሁበትን ሕዝብ ሁሉ፣
ፈጽሜ ባጠፋም እንኳ፣
አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም።
ተገቢውን ቅጣት እሰጥሃለሁ እንጂ፣
ያለ ቅጣት አልተውህም።”
Copyright information for AmhNASV